የፋሲል ከነማና የመቐለ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ አንድ ጨዋታ አስተናግዷል።

10 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማነ መቐለ ከተማ ተጫውተዋል።

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ የተካሄደው ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ባለፈው ሳምንት የቦታ ለውጥ ካደረገባቸው ሶስት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው።

ትናንት በተደረገ አንድ ጨዋታ ወልዲያ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይቷል።

ነገ ደግሞ ደደቢት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይገኛሉ።

በክልል ከተሞች ደግሞ ጅማ አባ ጅፋር ከመከላከያ፣ ወላይታ ድቻ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮ ኤሌትሪክ በተመሳሳይ 9 ዘጠኝ ሰአት የሚጫወቱ ይሆናል።

ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።