በፕሪሚየር ሊጉ ወልዲያና ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) 11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይካሄዳሉ።

በወጣው መርሀ ግብር መሰረት የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እንደሚከናወኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

ዛሬ በተደረገ አንድ የ11ኛው ሳምንት ጨዋታም ወልድያ ሼክ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታዲየም ወልዲያ ከተማ ከከቅዱስ ጊዮርጊስ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል።

ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ በአዲስ በአባ ስታዲየም ፋሲል ከነማ ኣነ መቐለ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ባለፈው ሳምንት የቦታ ለውጥ ካደረገባቸው ሶስት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው።

እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ደደቢት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ይገኛሉ።

በክልል ከተሞች ጅማ አባ ጅፋር ከመከላከያ፣ ወላይታ ድቻ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮ ኤሌትሪክ በተመሳሳይ ከ9 ዘጠኝ ሰአት የሚጫወቱ ይሆናል።

ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።