በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3 ለ 0 አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ.) ዛሬ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባጅፋር አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተዋል።

በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ አዳነ ግርማ አንድ ግብ እና አበባው ቡጣቆ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።