በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፏል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ጅማ ላይ ተካሂዷል።

ከቀትር በኋላ በተደረገው ጨዋታ ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ጅማ አባ ጅፋር ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዷል።

ባለፉት ጨዋታዎች ውጤት አልባ ጉዞ ሲያደርግ የቆየው ጅማ አባ ጅፋር በዛሬው ጨዋታ ድል ቀንቶታል።

በሜዳው ያደረገውን ጨዋታም 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የድል ጎሎቹንም ኦኪኪና ተመስገን ገብረኪዳን ማስቆጠር ችለዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ እንግዳ ቡድን ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ጅማ አባ ጅፋር ነጥቡን 7 ሲያደርስ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ባለበት 8 ነጥብ ረግቷል።