ቀነኒሳ በቀለ የህንድ ካልካታ የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በህንድ ካልካታ በዛሬው እለት የተካሄደውን የካልካታ ታታ ስቲል የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቀቀ።

ቀኒሳ በቀለ ውድድሩን 1 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በማግባትን በአንደኝነት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በዚህም የስፍራውን ከብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።
አትሌት ቀነኒሳ ከውደድሩ ቀደም ብሎ ባሳለፍነው ዓረብ በሰጠው መግለጫ በርቀቱ የግሉ ሰዓት የሆነውን 1 ሰዓት ከ12 ቀዲቃ ከ47 ሰከንድ ለማሻሻል እንደሚሮጥ ተናግሮ ነበር።

ሆኖም ግን ቀነኒሳ የግሉን ሰዓት ማሻሻል ባይቸልም፤ በህንዳዊው አትሌት ጎቪንዳን ላክሽማን የተያዘውን የስፍራውን ክብረ ወሰን በ3 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ በማሻሻል የግሉ አድርጓል።

በውድድሩ ኤርታራዊው አትሌት ፀጋይ ጥኡመይ 2ኛ፣ ታንዛኒያዊው አትሌት አጉስቲኖ ሱሌ 3ኛ፣ ህዳዊው አቪናሽ ሳብሌ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን ሲያጠናቅቁ፤ ኢትዮጵያዊው አትሌት አሰፋ ዲሮ 5ኛ ወጥቷል።

በሴቶች ምድብ የተካሄደውን የካልካታ ታታ ስቲል የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው 1 ሰዓት ከ26 ቀዲቃ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ በማግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።

degitu_hind.jpg

በዚህም አትሌት ደጊቱ አዝመራው የስፍራውን ክብረ ወሰን በ1 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ማሻሻል እንደቻለችም ተነግሯል።

አትሌት ደጊቱ አዝመራው በመከተልም ኬንያዊቷ አትሌት ሄላህ ኪፕሮፕ 2ኛ፣ ታንዛኒያዊቷ አትሌት ፋይሉና ማታንጋ 3ኛ፣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዲባቤ ኩማ 4ኛ ሲወጡ፥ ህዳዊቷ ሎጋናታን ሱሪያ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውደድሩን አጠናቃለች።

የህንድ ካልካታ ታታ ስቲል 25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ሲካሄድ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ነው።

ምንጭ፦ http://tsk25.procamrunning.in