በፕሪሚየር ሊጉ ደደቢትና ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለአሸናፊው ክለብ ግቧን ከመረብ ያሳረፈው ሙሉዓለም ረጋሳ ነው።

በሌላ በኩል 10 ሰዓት ላይ ደደቢት ከሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጫውተዋል።

በዚህም ደደቢት 5 ለ 2 ሲያሸንፍ አቤል ያለው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

ቀሪዎቹን የአሸናፊው ቡድን ግቦች ደግሞ ደስታ ደሙ እና ኤፍሬም አሻሞ ከመረብ አሳርፈዋል።

ለሲዳማ ቡና ከመሸነፍ ያላዳኑትን ሁለት ግቦች ያስቆጠሩት አዲስ ግደይ እና አብዱለጢፍ መሃመድ ናቸው።

ደደቢት ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 13 አድርሷል።

 

 

 

ምንጭ፦ሶከር ኢትዮጵያ