የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ የፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ እጩዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ የቀረበለትን የፕሬዚዳንት እና ስራ አስፈፃሚ እጩዎች ዝርዝር አፅድቋል።

ፌዴሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት ለፕሬዚዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡ

 

1. አቶ ጁነዲን ባሻ ቲሊሞ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን

2. አቶ ተካ አስፋው ተሰማ ከአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

3. አቶ ኢሳያስ ጂራ ቦሾ ከኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

4. ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ጋዮ ከደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

5. አቶ ዳግም መላሼን ዋኞክ ከጋምቤላ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን መወከላቸውን ኮሚቴው ገልጿል።

ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት እጩ ሆነው የቀረቡ፦

1. አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ አርጋው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን

2. አቶ ሰውነት ቢሻው ውቤ ከአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

3. አቶ አበበ ጋላጋይ ዘለቀ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን

4. አቶ ከማል ሁሴን መሃመድ ከኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

5. ዶክተር ሃይሊ ኢቲቻ ቡልቲ ከኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

6. አቶ ኢብራሂም መሃመድ ኢብራሂም ከሀረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

7. አቶ አብድረዛቅ ሀሰን መሃመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

8. ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙን ባበከር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

9. አቶ አሊሚራህ መሃመድ አሊ ከአፋር ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

10. ኮሎኔል አዎል አብድራሂም ኢብራሂም ከትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

11. ዶክተር ሲራክ ሃብተማርያም ከለለው ከአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

12. አቶ ወልደገብርሄል መዝገቡ ተስፋዬ ከትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

13. አቶ አስራት ኃይሌ ገብሬ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን

14. አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ሆርሳ ከደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

15. ዶክተር ቻን ጋትኮት ዮም ከጋምቤላ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

16. ኢንጅነር ሀይለኢየሱስ ፍስሃ አለማየሁ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ናቸው።

ኮሚቴው ተወዳዳሪነታቸው ያልፀደቁትን ዝርዝርም ጠቅሷል።

1. አቶ ሙራድ አብዲ ሀቢብ ከሀረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና

2. አቶ ልዑልሰገድ በጋሻው አስፋው ከኢትዮጵያ ዳኞች ማህበር ተወዳዳሪነታቸው እንዳልፀደቀላቸው ነው የገለፀው።

አስመራጭ ኮሚቴው ቅሬታ ያለው አካል ከህዳር 26-27 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ማቅረብ እንደሚችልም በመግለጫው ጠቁሟል።