የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ 12 አስመራጭ ኮሚቴዎችን መረጠ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉበኤው የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት እና ስራ አስፈፃሚዎችን የሚያስመርጡ 12 የኮሚቴ አባላትን መርጧል።

በአስቸኳይ ጉባኤው ላይ የተመረጡ የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከክልሎች እና ከማህብራት የተውጣጡ ናቸው።

የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ወር ሰመራ ላይ ለሚደረገው የፕሬዚዳንታዊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባለት ምርጫን የሚያስፈፅሙት የኮሚቴ አባላት ዝርዝር፦

1. አቶ በለጠ ዘውዴ- ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

2. አቶ መኮንን ደስታ- ከድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር

3. አቶ አብዱልሐኪም አብዱራህማን- ከሀረሪ ክልል

4. አቶ ዲዳ ድሪባ- ከኦሮሚያ ክልል

5. አቶ መሐመድ ያዮ- ከአፋር ክልል

6. አቶ አባዲ ሐድሽ- ከትግራይ ክልል

7. አቶ ፈረአን መሐመድ- ከሶማሌ ክልል

8. አቶ ዘሪሁን መኮንን- ከአማራ ክልል

9. አቶ ደርቤ ከበደ- ከቤንሻንጉል ክልል

10. አቶ ባንግ ሩዌዊ- ከጋምቤላ ክልል

11. ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው- ከደቡብ ክልል

12. አቶ ሸዋረጋ ደስታ- ከማህበራት ናቸው።

እነዚህ አባላት ምርጫውን በተገቢው ሁኔታ ለማስመረጥ ቃለ መሃላ የገቡ ሲሆን፥ ሶስት የቅሬታ ሰሚ አባላት እንደሚመረጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

አስቸኳይ ጉባኤው ምርጫው በሚከናወንበት ሂደት ዙሪያ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 29 እና 30 ቀን 2010 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል ተደርጎ የአስመራጭ ኮሚቴ ሳይመርጥና በምርጫው ሂደት ላይ ሳይወያይ መጠናቀቁ ይታወሳል።