በደልሂ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደው የደልሂ ግማሽ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።

በሴቶቹ ምድብ አትሌት አልማዝ አያና አሸናፊ ስትሆን፥ ውድድሩን 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ጨርሳለች።

በውድድሩ አባብል የሻነህ እና አትሌት ነጻነት ጉደታ አልማዝን ተከትለው ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

በወንዶቹ ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ለገሰ በ59 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ አሸናፊ መሆን ችሏል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አንዳምላክ በልሁ ደግሞ በአራት ሰከንድ ዘግይቶ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

ትውልድ ኬንያዊው ሊዮናርድ ኮሪር ደግሞ ኢትዮጵያውያኑን ተከትሎ 59 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ሶስተኛ ወጥቷል።

በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች የ27 ሺህ ዶላር ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

 

ምንጭ፦ www.news18.com/