በእንግሊዝ ፕሪምየር አርሰናል ቶትንሃም ሆትስፐርን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥሎው ተካሂደዋል።

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ አርሴናል ከቶተንሃም ሆትስፐር በሰሜን ለንደን ደርቢ 9 ሰዓት ተኩል ላይ በኢመሬትስ ስታዲየም ተካሂዷል።

በጨዋታውም ባለሜዳዎቹ አርሰናሎች ቶትንሃም ሆትስdፐርን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

በጨዋታው ላይም ሙስታፊ በ36ኛ ደቂቃ እንዲሁም ሳንቼዝ በ41ኛው ደቂቃ ላይ የአርሰናልን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።