በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ የምድብ ለ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

ቀትር ላይ የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክና መከላከያ ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

አመሻሽ ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ተገናኝተዋል።

ጨዋታውን ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ፥ አሜ መሃመድ ሁለቱንም የድል ጎሎች ማስቆጠር ችሏል።

አላዛር ፋሲካ ደግሞ ከእረፍት መልስ የአዳማ ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።

ከምድብ ሀ ኢትዮጵያ ቡና እና ጂማ አባ ጅፋር ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል።