በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ “ለ” ሁለቱም ጨዋታዎች በአቻ ተጠናቀዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ የምድብ “ለ” ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ አዳማ ከተማ ከመከላከያ 1 ለ 1 ተለያይተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ሲጋሩ የአዳማ ከተማው ደሳለኝ ደበሽ የጨዋታው ኮከብ ሆኗል።

አዳማ ከተማዎች በበረከት ደስታ ግብ አማካኝነት መሪ ቢሆኑም፥ የተሻ ግዛው መከላከያዎችን አቻ አድርጎ ሙሉ ጨዋታውን ያለሽንፈት አጠናቀዋል።

11 ሰዓት ከ30 የተደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታም በተመሳሳይ 1 ለ 1 አቻ አልቋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በካሉሻ አልሀሰን ግብ መምራት ቢችልም፥ ለፈረሰኞቹ ከሽንፈት የታደገቻቸውን ግብ አዳነ ግርማ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ዲዲዬ ሊብሬ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል።