በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዳል።

በቅድሚያ ስምንት ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደደቢት ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

በርካታ ደጋፊ ገብቶ ስታዲየም በተከታተለው ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፎታል።

ሳሙኤል ሳኑሚ ለኢትዮጵያ ቡና ሶስት ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ፥ ገናናው ረጋሳ ደግሞ ለአዲስ አበባ ከተማ የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል።