ጥሩነሽ ዲባባ በቺካጎ ማራቶን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንደሮው የቺካጎ ማራቶን በዛሬው እለት ተካሂዳል።

በርካታ አትሌቶች በተሳተፉበት ውድድር በሴቶች ምድብ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ድል ቀንቷታል።

ጥሩነሽ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመጨረስ አሸናፊ መሆን ችላለች።

ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ ሁለተኛ ስትሆን፥ አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሃሳይ በ35 ሰከንዶች ዘግይታ ሶስተኛ በመሆን ውድድሯን ጨርሳለች።

በወንዶቹ ምድብ ደግሞ አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ በ2 ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

ኬንያውያኑ ኪሩይ እና በርናርድ ኪፕየጎ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።


ምንጭ፦ chicagotribune.com