ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት የተለያዩ ጨዋታዎች ጨዋታዎች በዛሬው እለት ቀጥሎ እየተደረጉ ይገኛሉ።

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የሆነው የማንችስተር ሲቲ እና የሊቨርፑል ጨዋታም ኢትሃድ ስቴዲየም ላይ ከቀኑ በ8 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ተደርጓል።

በጨዋታም ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 5ለ0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል።

በጨዋታው ላይም ሴርጂዮ አጉዌሮ በ24ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ማንቸስተር ሲቲን መሪ ያደረገች ሲሆን፥ ገብርኤል ጂሰስ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ በተሰጠ ተጨማሪ ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ማንቸስተር ሲቲዎች የመጀመሪያውን አጋማሽ በመምራት አጠናቀዋል።

ከእረፍት መልስም ገብርኤል ጂሰስ በ53ኛ ደቂቃ ላይ 3ኛውን ጎል ለማንቸስተር ሲቲ ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን፥ ቀሪዎቹን ሁለት ጎሉች ሌሮይ ሳኔ በ77ኛው ደቂቃ እና መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመሪ 1ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

በዚህም ማንቸስተር ሲቲ 5ለ0 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ሊቨርፑልን መርታት ችሏል።

በጨዋታው ላይ የሊቨርፑሉ ሴይዶ ማኔ በ37ኛው ዲቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣ ሲሆን፥ ሊቨርፑልም ጨዋታውን በ10 ተጫዋቾች ለማጠናቀቅ ተገዷል።