በዳኛ ላይ ጥቃት ያደረሱ 9 የናይጄሪያ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዳኛ ላይ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ዘጠኝ የናይጄሪያ ተጫዋቾች እና ሁለት የእግር ኳስ ባለስልጣናት ላይ ቅጣት ተላለፈ።

በናይጄሪያ ሊግ የሚገኝ ክለብ ውስጥ የሚጫወቱት እያንዳንዱ ተጫዋቾች ላይም ከ12 እስከ 19 የሚደርስ የጨዋታ ቅጣት ነው የተጣለባቸው።

ተጫዋቾቹ ኤፍ.ሲ ኢፌይኒ ኡባህ ክለብ ውስጥ የሚጫወቱ ሲሆን፥ ባሳለፍነው ዓመትም ከእንግሊዙ ዌስትሃም ክለብ ጋር ከስምምነት ላይ ደርሶ ነበር።

ኤፍ.ሲ ኢፌይኒ ኡባህ የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾቹ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ በተደረገ ጨዋታ የእለቱ የመሃል ዳኛ ናኩራ አውዋል ኪንግ ኦሳንጋ የተባለን ተጫዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ በማስወጣታቸው ጥቃት አደርውባቸዋል ተብሏል።

በዚህ የተነሳም እያንዳንዱ ተጫዋች ከ12 እስከ 19 የሚደርስ የጨዋታ ቅጣት ተጥሎበቸዋል ነው የተባለው።

ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ የ4 ሺህ 900 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ