ዋልያዎቹ በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን አቻው ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ ተለያየ።

በሃዋሳ ከተማ በተደረገው ጨዋታ የሱዳን ብሄራዊ ቡድን በ76ኛው ደቂቃ ሰይፈዲን መኪ ባስቆጠረው ጎል ጨዋታውን 1 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።

አብዱራህማን ሙባረክ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ለዋልያዎቹ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ቡድኑ በቀጣዩ ሳምንት ዓርብ ሱዳን ላይ የመልስ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።