የአምናው ሻምፒዮን ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ ጉዞውን በሽንፈት ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017/2018 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘመን የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን ዛሬ ያደረገው ቸልሲ በበርንሌይ የ3 ለ 2 ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ በቼልሲዎች በኩል ካሂል በ14ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ፍራንሲስ ሴስክ ፋብሪጋስ ደግሞ በ84ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ ከሜዳ ተሰናብተዋል፡፡

ለበርንሌይ ግቦቹን ቮከስ በ24ና በ43ኛው ደቂቃ እንዲሁም ዋርድ በ39ኛ ደቂቃ በሰማያዊዎቹ መረብ ላይ አሳርፈዋል፡፡

የቼልሲን ሁለት ግቦች አልቫሮ ሞራታ እና ዴቪድ ሊዩዝ አስቆጥዋል፡፡

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጭ ከዋትፎርድ ጋር የተጫወተው ሊቨርፑል ደግሞ የውድድር ዓመቱን በአቻ ውጤት ጀምሯል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ሙሉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን 3 ለ 3 በማጠናቀቅ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

ለባለሜዳው ዋትፎርድ ኦካካ በ8ኛው ደቂቃ፣ ዳውኩሬ በ32ኛው ደቂቃ እንዲሁም ብሪቶስ 93ኛ ደቂቃ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

የሊቨርፑልን አቻ ግቦች ሰይዱ ማኔ በ29ኛው ደቂቃ፣ ፊልፕ ሪርሚኒሆ በ55ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምትና ሞሃመድ ሳላህ በ57ኛው ደቂቃ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

በዛሬው 11፡00 ሰዓት ላይ በተካሄዱ ሌሎች የጨዋታ መርሃ ግብሮች ዘንድሮ ሊጉን የተቀላቀለው ኸደርስፊልድ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 0፣ ኤቨርተን ስቶክ ሲቲን 1 ለ 0፣ ዌስትብሮም በርንማውዝን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ ሳውዝአምፕተን ከስዋንሲ ያልምንም ግብ ተለያይተዋል፡፡

በነገው ዕለት ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሃም እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ይጫወታሉ፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2017/208 የውድድር ዘመን ትናንት ምሽት ሲጀመር አርሰናል ሌሲስተር ሲቲን ገጥሞ 4 ለ 3 በመርታት በድል ጀምሯል፡፡

 

 

 

 

 

በምህረት አንዱዓለም