ኢትዮጵያ ጅቡቲን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 8፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2018 የቻን ውድድር ለማለፍ ከጀቡቲ ጋር ያደረገውን የማጣሪያ ጨዋታ 5 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ዋልያዎቹ እና የጂቡቲ አቻቸው የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በኤል ሃጂ ስታዲየም ነው፡፡

በዚህም  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡

ለዋልያዎቹ ጌታነህ ከበደ አራት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ ቀሪዋን ግብ ሙሉዓለም መስፍን አስቆጥሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ቡድን በ2018 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና(ቻን) የማጣያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጭ አድርጎ ደል ተቀዳጅቷል፡፡

ዋልያዎቹ፥ በቀጣዩ ሳምንት በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከጂቡቲ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት በጅቡቲ ከተሸነፈች ለሶስተኛ ጊዜ በቻን ውድድር ለመሳተፍ የምታደርገው ጉዞ ይገታል።

የኢትዮጵያ እና ጅቡቲን ብሔራዊ  ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009 ናይሮቢ ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ጅቡቲን 5 ለ 0 ማሸነፏ ይታወሳል።