ዋሊያዎቹ ለ2018 የቻን ውድድር ማጣሪያ ከጂቡቲ ጋር እየተጫወቱ ነው

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 8፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዋሊያዎቹ ለ2018 የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ ከጅቡቲ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጀምሯል።

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ጂቡቲ አቻው የመጀመሪያው  ጨዋታ በኤል ሃጂ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።

 

በ2018 በኬንያ አስተናጋጅነት በሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ በሚካሄደው የቻን ውድድር የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ዋልያዎቹ፥ በቀጣዩ ሳምንት በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከጂቡቲ ጋር የመልስ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

ፊፋ በሱዳን እግር ኳስ ላይ ጥሎት የነበረውን አገዳን ትላንት ማንሳቱ ይታወቃል።

በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ጅቡቲን ካሸነፈች በደርሶ መልስ የቡሩንዲን እና የሱዳንን አሸናፊ ትገጥማለች።

ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት በጅቡቲ ከተሸነፈች ለሶስተኛ ጊዜ በቻን ውድድር ለመሳተፍ የምታደርገው ጉዞ ይገታል ማለት ነው።

የኢትዮጵያ እና ጅቡቲን ብሔራዊ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009 ናይሮቢ ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ጅቡቲን 5 ለ 0 ማሸነፏ ይታወሳል።

በአንፃሩ ጅቡቲ በ2016 የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ ያደረገችው ጥረት በመጀመሪያው ዙር ተገቷል።

ቡቲ በደርሶ መልስ በቡሩንዲ 4 ለ 1 ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች።

 

ሃጂ ስታዲየም እየተካሄደ ነው