የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሄኒከን ኩባንያ ጋር የ30 ሚሊየን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሄኒከን ኩባንያ ጋር የ30 ሚሊየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ በዛሬው እለት የተፈረመ ሲሆን፥ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ መሆኑንም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፌዴሬሽኑ ከሄኒከን ኩባንያ ጋር የተፈራረመው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት በተለይም ከማልት ሶፊ ምርት ዘርፍ ጋር መሆኑም ታውቋል።

atheleticsa_sponsership_2.jpg

በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴና ምክትል ፕሬዚዳንት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያምን ጨምሮ የሄኒከን አመራሮች እና በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝነተዋል።