ደደቢት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በዛሬው የፍጻሜ ውድድር ላይ በሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ሀያላን የሆኑት ደደቢት እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫውተዋል።

በ10 ሰዓት ላይ የተደረገው ውድድርም በደደቢት 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በዚህም ደደቢት የ2009 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በደደቢት የተረታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውድድሩን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ አዳማ ከተማ ከሃዋሰ ከተማ ተጫውታል።

ጨዋታውም በአዳማ ከተማ 2ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ አዳማ ከተማም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግን በሶስተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድርም በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በፕሪምየር ሊጉ ሃዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፍጻሜ የተፋለሙ ሲሆን፥ መደበኛው የጨዋታ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ ነበር።

ሆኖም ግን ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመለያ ምቶች 4ለ2 በመርታት ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

ይህንን ተከትሎም ሀዋሳ ከተማ የ2009 ዓ.ም 17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒየን ሆኗል።

ፕሪምየርሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ 2ኛ ነመሆን ሲያጠናቅቅ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ኛ፣ አዳማ ከተማ 4ኛ ደረጃን ይዘዋል።