ፖቸቲኖ የሚያዚያ ወር የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ማውሪዮ ፖቸቲኖና የሚያዚያ ወር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ አሰልጣኝ ምርጫን አሸነፉ።

የቶተንሃሙ ሰን ሂዊንግ ሚን ደግሞ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።

ቶተንሀም በወሩ ያደረጋቸውን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለ ሲሆን፥ 16 ጎሎችን አስቆጥሮ አንድ ብቻ ተቆጥሮበታል።

የቡድኑ አሰልታኝ ማሪዮ ፖቸቲኖ በውድድር አመቱ ኮከብ ተብለው ሲመረጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አጥቂው ሰን ሂዊንግ ሚን በወሩ አምስት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ለሽልማቱ የቡድን አጋሮቹን አመስግኗል።

ደቡብ ኮሪያዊው አጥቂ ይህን ሽልማት ሲያገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ቶተንሀም ሆትስፐርስ በፕሪሚየር ሊጉ 2ኛ ደረጃን ይዞ የማጠናቀቅ ሰፊ እድል አለው።

 

 


በዘላለም ተፈሪ