በኤፍ ኤ ካፑ ቼልሲ እና አርሰናል ለፍጻሜ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ የኤፍ ኤ ካፕ አርሰናል የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

ትናንት ምሽት በኤሚሬትስ ማንቼስተር ሲቲን ያስተናገዱት መድፈኞቹ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ከቼልሲ ጋር በፍፃሜው የሚጫወተው።

ማንቼስተር ሲቲ በሰርጂዮ አጉየሮ በ62ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢጀምርም ናቾ ሞንሪያል መድፈኞቹን ከዘጠኝ ደቂቃ በኋላ አቻ አድርጓል።

አሌክሲስ ሳንቼዝ ደግሞ በጭማሪ ሰዓት አርሰናልን የፍፃሜ ተፋላሚነት የምታረጋግጥ ጎል ከመረብ አገናኝቷል። 

ከትናንት በስቲያ ቼልሲ በዌምብሌይ ስታዲየም ቶተንሃም ሆትስፐርን  4 ለ 2 ድል ማሸነፋቸው ይታወሳል።

በመሆኑም ቼልሲ ከአርሰናል የሚያደርጉት የፍፃሜ ፍልሚያ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

አርሰናል በአርሰን ቬንገር አማካኝነት ስድስት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አንስቷል።

መድፈኞቹ 20 ጊዜ ለኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል።