በቦስተን ማራቶን ኬንያውያኑ የበላይ ሆነዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አመታዊው የቦስተን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች በኬንያዎች አሸናፊነት ተጠናቋል።

ትናንት ምሽት በተካሄደው ውድድር ኬንያውያኑ የበላይ ሲሆኑ፥ በወንዶች ጎፍሬይ ኪሩይ አሸናፊ ሆኗል።

ጎፍሬይ ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ጨርሶታል።

አሜሪካዊው ጋሎን ሩፕ ሁለተኛ ሲሆን፥ ጃፓናዊው ሱጉሩ ኦሳኮ ደግሞ በሶስተኝነት አጠናቋል።

ኢትዮጵያዊው ዲኖ ስፍር ስምንተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል።

በሴቶች የተካሄደውን ውድድር ደግሞ ኤድና ኪፕላጋት በበላይነት አጠናቃለች።

ኪፕላጋት ርቀቱን 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃለች።

ባህሬንን የወከለችው ሮዝ ቼሊሞ ሁለተኛ አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሃሳይ ደግሞ ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

ብዙነሽ ዳባ ስምንተኛ እንዲሁም ሩቲ አጋ ደግሞ 10ኛ ሆነው ጨርሰዋል።

አፀደ ባይሳ በሴቶች ለሚ ብርሃኑ በወንዶች የአምናው የቦስተን ማራቶን አሸናፊዎች ነበሩ።