በቻምፒየንስ ሊግ ፒ ኤስ ጂ ባርሴሎናን በሰፊ የጎል ልዩነት ረታ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምሯል።

በትናንት ምሽት በተደረገው የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ በስታድ ደ ፕሪንስ ፓሪስ ሴንት ጀርመን፥ የካታላኑን ባርሴሎና አስተናግዷል።

demaria_2.jpg

በዚህም ፓሪስ ሴንት ጀርመን የካታላኑን ባርሴሎናን 4ለ0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታውም ፓሪስ ሴንት ጀርመን ዲማሪያ በ18ኛው እና በ55ኛው ደቂቃ ሁለት ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል። 

ቀሪውን ሁለት የማሸነፊያ ጎሎች ድላክሰር በ40ኛው ደቂቃ እንዲሁም ኤዲሰን ካቫኒ በ71ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

demaria_1.jpg

በሌላኛ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ደግሞ ስታዲዮ ዳሉዝ ላይ ቤኔፊካ ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ተጫውተዋል።

ጨዋታውም በቤኔፊካ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው ላይ የቤኔፊካን የማሸነፊያ ጎል ኮስታስ ሚትሮግሉ በ41ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

benefica_1.jpg

በዛሬው እለት ሪያል ማድሪድ በበርናባው ናፖሊን ሲያስተናግድ፥ አልያንዝ አሬና ላይ ደግሞ ባየርን ሙኒክ ከአርሰናል ይገናኛሉ።

ሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ እና ረቡዕ ይካሄዳሉ።

android_ads__.jpg