ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊጉ መሪ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 አጥብቧል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ አንድ ጨዋታ ተደርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልዲያ ከነማን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

አቡበከር ሳኒ በ74ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን በአንድ ነጥብ በልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከመሪው አዳማ ከተማ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነትም ወደ 1 አጥብቧል።

ወልዲያ ከተማ በበኩሉ በ10 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፕሪሚየር ሊጉን አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ይመራል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ20፣ ደደቢት በ19፣ አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ፋሲል ከተማ በ18 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ7፣ ሀዋሳ ከተማ በ6 እንዲሁም አዲስ አበባ ከከተማ በ5 ነጥብ በወራጅ ቀጠናው ውስጥ ይገኛሉ።

ኮከብ ግብ አግቢነቱን ደግሞ ጌታነህ ከበደ በ10 ጎሎች ሲመራ፤ አዳነ ግርማ በ5 ተከታዩን ደረጃ ይዟል።

 

 

በፋሲካው ታደሰ