ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያውን የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ፖርቹጋላዊው ክርስትያኖ ሮናልዶ የአለም አቀፉ እግርኩዋስ ማህበር /ፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት አሸንፏል።

የፊፋ ምርጦች /FIFA best award/ የመጀመሪያ ዙር ሽልማት ትናንት ምሽት በሲዊዘርላንድ ዙሪክ ተካሂዷል።

በዚህ ስነ ስርዓት ላይ ባለፈው የውድድር አመት ከክለቡ ጋር የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን እንዲሁም ከብሄራዊ ቡድኑ ፖርቱጋል ጋር የአውሮፓ ዋንጫን ያነሳው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፊፋ ምርጥነት ሽልማቱን ተቀብሏል።

በዚህም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአመቱ 4ኛ የግል ሽልማቱን ማግኘት ችሏል።

በፊፋ ምርጦች ሽልማት ላይ ሊዮኔል ሜሲ ሁለተኛ ሲሆን፥ አንቶዋይን ግሪዝማን ደግሞ ሶስተኛ በመሆን ተመርጠዋል።

በሴቶቹ ዘርፍ ደግሞ የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋችዋ ካርሊ ሊዮልድ የፊፋ ምርጥ ሽልማትን ማግኘት ችላለች።

women.jpg

በምረጥ የአመቱ አሰልጣኝ ዘርፍ የሪያል ማድሪዱ ዚነዲን ዚዳን፣ የሌስተር ሲቲው ክላውዲዮ ራኔሪ እንዲሁም የፖርቱጋል ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፌርናንዶ ሳንቶስ እጩ በመሆን ቀርበዋል።

በዚህም ከሌስተር ሲቲ ጋር ሳይታሰብ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያነሱት ክላውዲዎ ራኔሪ ምርጥ ተብለዉ በመመረጥ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

raneri_h.jpg

ፊፋ ቡሽካሽ አልያም የአመቱ ምረጥ ጎል የሚለውን ዘርፍ ደግሞ ማሌዢያዊው ሞሃድ ፋውዚ ባለፈዉ አመት ባስቆጠራት የቅጣት ምት አሸንፏል።

የአመቱ ምርጥ 11 ቡድንም በዚሁ ስነ ስርዓት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ማኑኤል ኑዌር፣ ዳኒኤል አልቬስ፣ ጄራርድ ፒኬ፣ ሴርጂዮ ራሞስ፣ ማርሴሎ፣ ቶኒ ክሩስ፣ ሉካ ሞድሪች፣ አንድሬስ ኢኔስታ፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና አንቱዋን ግሪዝማን በቡድኑ ውስጥ መካተት ችለዋል።

አዲስ ዘርፍ በሆነው የአመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ሽልማት የሊቨርፑልና ቦሪስያ ዶርትሙንድ ደጋፊዎች በጋራ ተመርጠዋል።


በኢዩኤል ዘሪሁን

android_ads__.jpg