5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በባህር ዳር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከጥር 5 እስከ ጥር 9 2009 ዓ.ም በባህር ዳር ይካሄዳል።

በሻምፒዮናው እድሜያቸው 18 እና 19 የሆናቸው ወጣት አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ እድሜያቸው 16 እና 17 የሆናቸው ታዳጊዎችም መካፈል ይችላሉ ብሏል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን።

የእርምጃ ውድድርን ጨምሮ ከ20 የሚበልጡ የአትሌቲክስ ውድድሮች በሻምፒዮናው የሚካሄዱ ይሆናል።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊወክሉ የሚችሉ ውጤታማ አትሌቶች እየተመረጡ ውጤታማ እየሆኑበት ይገኛሉ ነው ያለው ፌዴሬሽኑ።

የዘንድሮው 5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መጋቢት 2017 በአልጀሪያ ኡራን ለሚካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ወጣት አትሌቶች ይመረጡበታል።

ሻምፒዮናው በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች ውስጥ ለሚገኙ ወጣት አትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር እና ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ታምኖበታል።

 


በፋሲካው ታደሰ

 

android_ads__.jpg