ካፍ ሪያድ ማህሬዝን የአፍሪካ የ2016 ምርጥ ተጫዋች አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሌስተር ሲቲው አጥቂ ሪያድ ማህሬዝ የአፍሪካ እግር ኳር ኮንፌደሬሽን (ካፍ) የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።

የ25 አመቱ አልጀሪያዊ ባለፈው አመት ሌስተር ሲቲ ዋንጫ እንዲያነሳ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

ማህሬዝ በቢቢሲ የ2016 የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ተጫዋች ምርጫ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።

በ2016 ሶስት ሽልማቶችን የወሰደው ሪያድ ማህሬዝ በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጡም አይዘነጋም።

የቦርሲያ ዶርትሙንዱ ጋቦናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ፔር ኢምሪክ ኡቤሚያንግ ከማህሬዝ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ደግሞ በካፍ ሶስተኛ ሆኖ ተመርጧል።

የአርሰናሉ አሌክስ ኢዎቢ ደግሞ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ወስዷል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

android_ads__.jpg