ስፖርት

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2014 የዓለም ዋንጫ ዛሬ በብራዚል ቀጥሎ በደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚዎች የነበሩት የስፔንና ሆላንድ ትንቅንቅ ዛሬ ምሽትም እንዲጠበቅ ሆኗል ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ብራዚል ለሁለተኛ ጊዜ የምታስተናግደው 20ኛው የአለም ዋንጫ በብራዚል አስተናጋጅነት በድምቀት ተጀምሯል።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ብራዚል ለሁለተኛ ጊዜ የምታስተናግደው 20ኛው የአለም ዋንጫ ዛሬ ምሽት ይጀመራል።

በመክፈቻው ጨዋታ አስተናጋጇ ብራዚል ክሮሺያን በሳኦ ፖሎ አሬና ደ ሳኦፖሎ ወይም አሬና ኮሮንቲያስ ተብሎ በሚጠራው ስታዲየም ትገጥማለች።

ይህን የመክፈቻ ጨዋታ የ42 ዓመቱ ጃፓናዊ ዩቺ ኒሺሙራ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል።

የስፖርት አፍቃሪያንና የአለም ህዝብ ሁሉ የውድድሩን መጀመር በታላቅ ጉጉት እየጠበቀ ነው።

በስምንት ምድብ የተደለደሉ 32 ብሔራዊ ቡድኖች ለአንድ ወር የሚያደርጉት  ፉክክር በብራዚል 12 ከተሞች ይስተናገዳሉ።

የፍጻሜው ጨዋታ ደግሞ በ1950ው የአለም ዋንጫ ብራዚል በፍጻሜ ጨዋታ በኡራጓይ ተሸንፋ ዋንጫ ባጣችበት በሪዮ ዴ ጄኔሪዮ ከተማ በሚገኘው ግዙፉ ማራካኛ ስታዲየም ይደረጋል።

ባለፉት ጊዜያት በአለም ዋንጫ መድረኮች ላይ በርካታና አይረሴ አወዛጋቢ የጎል ውሳኔዎች የታዩ ሲሆን ፥ በብራዚሉ የአለም ዋንጫ ግን መሰል ድርጊት እንዳየፈጠር  የጎል መስመር ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ሞሮኮ ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ለብሄራዊ ቡድኑ የሚሰለፉ ተጫዋቾችን ለመለየት በመጀመሪያ ማጣሪያ ውስጥ የተካተቱትን ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ አደረጉ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2006(ኤፍ.ቢ.ሲ.)  የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ነገ ጠዋት ወደ ጋና ያመራል።