የምልክት ቋንቋ የምትችለዋ ኮኮ ጉሬላ በ46 ዓመቷ አረፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ግዛት የምልክት ቋንቋ አጥርታ የምታውቀው ኮኮ በመሰኘት የምትታወቀው ጎሬላ በ46 ዓመቷ አረፈች፡፡

ኮኮ ከ1 ሺህ በላይ የአሜሪካን የምልክት ቋንቋዎችን አጥርታ መናገር ትችል ነበር ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ኮኮ አንዳንድ የንግግር ቃላትንም መረዳት እንደምትችል ተነግሯል፡፡

የኮኮ አሳዳጊዎች እንደ ቤት እንስሳ ሲሆን ያሳደጓት ኦልቦል የምትሰኝ ድመትም አብራት ትኖር እንደነበር ተነግሯል በላም ሌሎች ሁለት ድመቶቸንም ማሳደግ ጀምራ ነበር፡፡

የጎሬላ ማዕከል ፋውንዴሽን የኮኮ ማረፍን ተከትሎ ባለ ድንቅ ችሎታዋ ኮኮ የጎሬላዎች ሁሉ አምባሳደር እንደነበረች በመግለጫቸው አስፍረዋል፡፡

ያላት የአዕምሮ ችሎታ ወይንም የአይኪው ብቃት ከ75 እስከ 95 ሲሆን፥ የሰው ልጅ ከ85 እስከ 115 ይጠጋል አማካዩ አይኪው ደግሞ 100 መሆኑ ተግልጿል፡፡

ኮኮ የተወለደችው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ971 ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው የእንስሳ ማቆያ ማዕከል ሲሆን፥ ዶክተር ፓተርሰን በቀጣዩ ዓመትም የምልክት ቋንቋ እንዳስተማሯት ተገልጿል፡፡

 

 

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ