ከአልኮል የሚዘጋጀው አይስክሬም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 13፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአልኮል የተዘጋጀው እና ሰዎች እንዲሰከሩ ሊያደርግ የሚችል አይስክሬም መዘጋጀቱ ተነገረ።

ይህ አይስክሬም ከአዲስ ፍራፍሬ እና አረቂ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ይህም ከሌሎች የአይስክሬም አይነቶች በተለየ ሁኔታ ከአልኮል የተዘጋጀ እንዲሆን አድርጎታል።

በተጠቃሚዎቹ ዘንድ ባለአልኮሉ አይስክሬም ተብሎ የሚጠራውና ሲሆን ከቢራ ጋር ሊነፃፀር የሚችል የአልኮል መጠን እንዳለው ተነግሯል።

እንድ ቢራ 4 ነጥብ 5 በመቶ የአልኮል መጠን ሲኖረው አይስክሬሙ ደግሞ 15 በመቶ የአልኮል መጠን ያለው ሲሆን፥ ይህም ሰዎችን ለስካር እንደሚዳርግ እና ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስወጣ ተነግሯል።

አይስክሬሙ ከአልኮል የሚዘጋጅ ከመሆኑ በተጨማሪ ስምንት ፍሬ አይስክሬም ለመግዛት 99 ነጥብ 99 የአሜሪካ ዶላር ማውጣት ያስፈልጋል።

ባለአልኮሉን አይስክሬም አሜሪካውያን በሬስቶራንቶች፣ሱቆች እንዲሁም በድረ ገፅ መገበያያዎች ማግኘት የጀመሩ ሲሆን፥ ስምንት የተለያዩ ቃናዎች እንዳሉት ተነግሯል። 

ምንጭ፦ ኦዲቲሴንትራል