የአለም ዋንጫን ተከትሎ የተጫዋችን ምስል በፀጉር ላይ የሚነቅሰው ፀጉር አስተካካይ

አዲስ አበባ፣ሰኔ፣ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩሲያ ሚካሄደውን አለም ዋንጫ ተከትሎ ተመልካቾች በሚወዷቸው ተጫዋቾች ምስል ቅርፅ ወይም ንቅሳት ፀጉራቸውን ማሳመር የሚችል ባለሙያ ከወደ ሰርቢያ ብቅ ብሏል፡፡

ማሪዎ ሀቫላ ተባለው ፀጉር አስተካካይ የሜሲ እና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ምስሎችን በአድናቂዎቻቸው የእራስ ቅል ጀርባ እነቀሰ እንደሚያሳምር ተነግሯል፡፡

ፀጉር አስተካካዩ ከእግር ኳስ ተጫዋቾች ምስል በተጨማሪ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሌሎች ፖለቲከኞች ምስል ይነቅሳል ተብሏል፡፡

ይህን ስራ በሚሰራበት ወቅት የተጫዋቹን ምስል ወይም ቅርፅ ማውጣት አስቸጋሪው ስራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡kim_1.jpg

የተጫዋቾችን ምስል ለመንቀስ ከአምስት እስከ ሰባት ሰዓት የሚፈጅበት ሲሆን የክሪስቲያኖን ምስል በነቀሰበት ወቅት ከበርካቶች አድናቆት እንደደረሰው ተናግሯል፡፡

ንቅሳቱ ፀጉር እያደገ የሚሄድ በመሆኑ ከ10 ቀን በኃላ የምስሉ ጥራት እቀነሰ እንደሚሄድና ተነቃሾች 132 አሜሪካ ዶላር ማውጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ምንጭ፡-ስካይኒውስ