የአለም ዋንጫ እንግዶቻቸውን በወዳጅነት ለመቀበል ፈገግታን መማር ግድ የሆነባቸው ሩሲያውያን

አዲስ አበባ፣ሰኔ፣6፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያውያን የአለም ዋንጫን ለመታደም ወደ ሀገሪቱ የሚያቀኑ እንግዶችን በወዳጅነት መቀበል እንዲችሉ የሳቅና ፈገግታ ጥበብን መሰልጠናቸው ተነግሯል።

ሩሲያ በአለም ፊታቸው ላይ የሳቅ ወይም የፈገግታ ስሜትን ከማያሳዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይመደባሉ።

በዚህ ምክንያት ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ወደ ሩሲያ የሚያቀኑ ሰዎች ሩሲያውያን በወዳጅነት የማይቀርቡ ብለው የሚገልጿቸው በመሆኑ አመለካከቱን ለመቀየር ይህ የሳቅ እና ፈገግታ ጥበብ ስልጠና እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

በሩሲያ አዘጋጅነት የሚካሄደውን የአለም ዋንጫ የሚታደሙ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቱሪስቶች ወደ ሀገሪቱ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

ዩሊያ ሜላሜድ የተባለች ግለሰብ በሩሲያ ውስጥ ሳቅ ወይም ፈገግታ አደጋ ነው በማለት የገለፀች ሲሆን፥ በመንገድ ላይ ፈገግታን በማሳየቷ ፖሊሶች እንዳስቆሟት ተናግራለች።

በወቅቱም ለምን እንዳስቆማት ስትጠይቅ በመንገድ ላይ በመሳቋ ምክንያት መሆኑን የፖሊስ አባል አንደገለፀላት ታስታውሳለች።

በአጠቃላይ ለሩሲያውያን በመንገድ ላይ መሳቅ ወይም ፈገግታ ማሳየት ያልተለመደ እና ሰዎች እንዲጠራረጡ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

በዚህ ምክንያት የሳቅና ፈገግታ ትምህርቱ ለባቡር ጣቢያ ሰራተኞችና በየአለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር የሚያሰራቸው ሩሲያውን እንደተሰጠ ተጠቁሟል። 

ሩሲያ የምታሰተናግደወ 21ኛው የአለም ዋንጫ ከነገ ጅመሮ መካሄድ ይጀምራል።

ምንጭ፦ ፎክስኒውስ