ልብ ለጋሽ እስኪያገኝ ከ1ዓመት በላይ ከሆስፒታል ውጭ በሰው ሰራሽ ልብ የቆየው አሜሪካዊ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ4፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ስታን ላርኪን የተባለው የ25 ዓመት ወጣት ከአንድ ዓመት በላይ ከሆስፒታል ውጭ በሰው ሰራሽ ልብ ከቆየ በኋላ የተሳካ የልብ ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል ተብሏል።

ላርኪን በዚህ ቴክኖሎጂ ህይወቱን እንዲያቆይ የተገደደው ልቡ ስራዋን በማቆሟና በጊዜው ልብ ለጋሽ ሊጋኝ ባለመቻሉ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

 ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ሲል የልብ ህሙማን በድንገት ልባቸው ስራውን ሲቋርጥ ለማገዝ የሚያስችል ሲሆን፥ ሙሉ በሙሉ በህይወት ለማቆየት በቂ ያለመሆኑንም የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

የላርኪንን የልብ ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና ልዩ የሚያደርገው ከአንድ ዓመት በላይ በሰው ሰራሽ ልብ የቆየ ሲሆን፥ ሌሎቹ የልብ ህሙማን ወዲያውኑ ንቅለ ተከላው የሚደረግላቸው መሆኑ ነው ተብሏል።

ላርኪን ጊዜአዊ ሰውሰራሽ ልብ ከተተካለት በኋላ ከሆስፒታል ውጭ በመቆየት ትክክለኛው የልብ ንቅለ ተከላ እስኪሰራለት በህይወት በመቆየትም የመጀመሪያው እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ከሰው ሰራሽ ልቡ ጋር ተያያዥነት ያለው 6 ኪ/ግራም ያህል ክብደት የሚመዝብ መሳሪያ በጀርባው ይዞ ይቀሳቀስ የነበረ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።

ሌሎች የላርኪን አይነት ህሙማን ትክክለኛው የልብ ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና እስኪደረግላቸው በሆስፒታል እንዲቆዩ የሚደረግ ሲሆን፥ ላርኪን ከሆስፒታል ውጭ የቆየ መሆኑም ተገልጿል።

ግለሰቡ ከ2 ሳምንት በፊት በሚችጋን ዩንቨርሲቲ ፍራንከል የልብ ጤና ማዕከል የተሳካ የልብ ንቅለ ተከላ ህክምናው የተሰራለትና አሁን ላይ ሙሉ ጤንነት የሚሰማው መሆኑን ገልጿል።

ይህ ወጣት በዩንቨርሲቲዎች በመዘዋዎር የህወት ተሞክሮውን በማከፈል በዘርፉ ባለሞያዎች ዘንድ እውቅና እና አድናቆትን እንዳተረፈም ነው የተገለጸው።

አሁን ላይ 5ነጥብ7 ሚሊየን ያህል ዜጎች የለልብ ህሙማን ሲሆኑ 10 በመቶ ያህሉ ለከባድ ችግር የተጋለጡ መሆኑናቸውን የአሜሪካ የልብ ማህበር መረጃ አመላክቷል።

 

 

ምንጭ፦ sciencedaily.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ