የዓለም ቅንጡ ተሽከርካሪዎች አውደ ርዕይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለማችን ቅንጡ ተሽከርካሪዎች አውደ ርዕይ በእንግሊዟ ለንደን ከተማ ተዘጋጅቷል።

የ2018 የዓለማችን ቅንጡ ተሽከርካሪዎች አውደ ርዕዩ ባሳለፍነው ሀሙስ ነው በለንደን ከተማ በይፋ ለጎብኚዎች ክፍት የተደረገው።

በአውደ ርዕዩ ላይም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ 125 ውድ የሆኑ ቅንጡ ተሽከርካሪዎች ለእይታ እንደቀረቡም የአውደ ርዕዩ አዘጋጆች አስታውቀዋል።

car_3.jpg

በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የቀረቡት ተሽከርካሪዎችም፣ ፈጣን፣ በጣም ፈጣን፣ እጅግ በጣም ፈጣን እና በሌሎች አይነቶች የከፋፍለው ነው የቀረቡት።

car_5.jpg

በአውደ ርዕዩ ላይም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የ1911 ፊያት S76፣ የ1965 ጃጉዋር E-ታይፕ፣ የ1954 ሜርሴዲስ ቤንዝ 300 SL እና የ1996 ፌራሪ F50 ምርቶች እንደቀረቡም ተነግሯል።

car_2.jpg

ምንጭ፦ CGTN