በ42 አመት ውስጥ 30 ሺህ “ቢግ ማክ” በርገሮችን የተመገበው ግለሰብ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶን ጎረስኬ የተባለው ግለሰብ ከፈረንጆቹ 1972 ጀምሮ 30 ሺህ “ቢግ ማክ” በርገሮችን መመገቡን አስታወቀ።

30 ሺህኛውን የቢግ ማክ በርገርን በተመገበበት ወቅትም ይህም በህይወቱ ትልቁ ስኬት እንደሆነና ሲናፍቀው የነበረ ጉዳይ መሆኑን ተናግሯል።

ግለሰቡ ፎንድ ዱ ላክ በተሰኘው በርገር ቤት ክብረወሰን ሆኖ የተመዘገበውን “ቢግ ማክ” በርገር ሲመገብ በርካቶች እንደተከታተሉት ታውቋል።

ዶን ጎረስኬ ለመጀመሪያ ጊዜ በፎንድ ዱ ላክ የምግብ አምራች በተገኘበት ወቅት የበሬ ስጋን ከሰላጣ፣ ሽንኩርት እና ለምግብ ልዩ ቃና የሚሰጥ ጣፋጭ ቅመም የተጨመረበት በርገር እንደተመገበ ነው ያስታወቀው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በፎንድ ዱ ላክ በተገኘበት ወቅት ዘጠኝ ቢግ ማክ በርገሮች የተመገበ ቢሆንም በጊዜው በቂ በርገር እንዳልተመገበ ተሰምቶት እንደነበር አስታውሷል።

ጎረስኬ የትዳር አጋሩን እንድታገባው በማክዶናልድ የመኪና ማቆያ ስፍራ ጥያቄ እንዳቀረበ ነው 30 ሺህኛውን በርገር በተመገበበት ወቅት ለተሰበሰቡ ሰዎች ተናግሯል።

በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ደረሰኞችን እና የበርገር መያዥ እቃዎችን ሰብሰቦ እንደነበር ያስታወቀ ቢሆንም ብዙ መሰብሰብ ያለበት አዝናኝ መረጃዎች በመኖራቸው በ1990 አካባቢ 7 ሺህ የሚጠጉ ካርቶኖችን ማስወገዱን ገልጿል።

ማክዶናልድ በድረ-ገፁ በአንዱ “ቢግ ማክ” በርገር 540 ካሎሪስ እና 28 ግራም የስብ መጠን መኖሩን ያስታወቀ ቢሆንም ጎረስኬ በቅርቡ ባደረገው የህክምና ምርመራ በሰውነቱ ያለው ኮሌስትሮል ዝቅተኛ እንደሆነ እና የደም ግፊቱ ትክክለኛ እንደሆነ ማረጋገጥ ችሏል።

በአመጋገቡ ሰዎች እንደሚስቁበት ያስታወቀው ጎረስኬ ሲሆን፥ በዚህ ምክንያት ምንም አይነት ቅሬታ እንደማይሰማውን እና እንደማያዝን ነው ያስታወቀው።

ከስራ በኋላ ቢግ ማክ በርገር በመኖሩ ምክንያት ምግብ እንደማያዘጋጅ እና ፈጥኖ የሚደርስ በመሆኑ ምርጫው እንደሆነ ተናግሯል።

በህይወት ዘመኑም ረዥም መንገድ መኪና ባሽከረከረበት ወቅት እና እናቱን በሞት ያጣበት ጊዜ በርገር ሳይመገብ ያዋለባቸው ሁለቱ ቀናት መሆናቸውን ገልጿል።

ምንጭ፦ስካይኒውስ