የ69 አመቱ ቻይናዊ በሰው ሰራሽ እግር ታግዘው ኤቨርስት ተራራን መውጣት ችለዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዢያ ቦዩ የ69 አመት ቻይናዊ አዛውንት ናቸው።

ግለሰቡ ከፈረንጆቹ 19 75 ጀምሮ ረጅሙን የኤቨርስት ተራራ ለመውጣት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገዋል።

ተራራውን ለመውጣት ባደረጉት ሙከራ ግን ከጉዳት የዘለለ ነገር አላተረፉም።

የመጀመሪያ ሙከራቸውን ባደረጉበት በዚያው አመት ታዲያ፥ ለከፋ ጉዳትም ተዳርገዋል።

በወቅቱ ተራራውን እየወጡ በነበረበት ወቅት እጅግ ቀዝቃዛና በረዷማው ክፍል ላይ ሲደርሱ፥ አብሯቸው ይጓዝ ለነበረ የቲቤት ዜጋ ለብርድ

መከላከያና በምሽት ወቅት ለመኝታ የሚጠቀሙበትን አልባሳት ይሰጡታል።

mount_climber_1.png

በዚህ ሳቢያም ሌሊቱን ሙሉ ለከፍተኛ ቅዝቃዜ ተዳርገው በዚህ ሳቢያም ይጎዳሉ።

የቅዝቃዜው ውጤት ባስከተለው ችግርም ሁለት እግሮቻቸውን አሳጥቷቸው ከዚያ በኋላ በሰው ሰራሽ እግሮች ለመንቀሳቀስ ተገደዋል።

ይህ ቢሆንም ግን ረጅሙን ተራራ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት አላቋረጡም ነበር።

በዚህ መልኩ ለ45 አመታት ሙከራ አድርገዋል፤ በፈረንጆቹ 2013 እና 2015 በአካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥና የበረዶ ናዳ ሳቢያ ሙከራቸው አልተሳካም።

በ2016 ደግሞ እጅግ ከባድ በሆነ ቅዝቃዜ ሳቢያ መንገዳቸውን አቋርጠው ለመመለስ ተገደዋል።

በሁኔታው ተስፋ ያልቆረጡት ቦዩ ከበርካታ ሙከራዎች በኋላ በትናንትናው እለት ረጅሙን ተራራ የመውጣት አቅዳቸውን አሳክተዋል።

ለዚህ ስኬታቸው ደግሞ ሼርፓስ እየተባሉ የሚጠሩት የቲቤት ጎሳዎች እገዛ አስፈልጓቸዋል ተብሏል።

የእርሳቸው ፅኑ ፍላጎት ከሼርፓሶች የተራራ አወጣጥ ክህሎት እና ችሎታ ጋር ተዳምሮ የአዛውንቱን እቅድ አሳክቷል።

ሁለት እግራቸውን ያሳጣቸውን ቅዝቃዜ ተቋቁመው ለ45 አመታት ያደረጉት ጥረት በመጨረሻም በስኬት ተጠናቋል።

 

 

ምንጭ፦ ፒፕልስ ደይሊ ቻይና