በነፃ በተሰጠው የሎተሪ ትኬት 4 ነጥብ 38 ሚሊየን ዶላር ያሸነፈው አሜሪካዊ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊው ግለሰብ ለማስታወቂያ በሚል በነፃ በተሰጠው የሎቶ ሎተሪ ትኬት 4 ነጥብ 38 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማሸነፉ ተሰምቷል።

ቻክ አንደርሰን የተባለው አሜሪካዊው ግለሰብ ባሳለፍነው ሀሙስም በአሜሪካዋ ሎዋ ወደሚገኘው የሎተሪ አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት በመሄድ እድለኛ መሆኑን መግለፁም ተነግሯል።

ቻክ እድልኛ የሆነውም የሎቶ ቁጥሮቹን ማለትም 8-15-18-32-45 በማገጣጠም እና አንድ ኮከብ ኳስ በማግኘቱ ነው ተብሏል።

ቻክ አንደርሰን የሎቶ ሎተሪ የጫወት ሀሳብ ኖሮት እንደማያውቅ የተናገረ ሲሆን፥ ወደ ሱፐር ማርኬት በመሄድ እቃ በሚገዛበት ጊዜ የሎተሪ ትኬቱ በማስታወቂያ መልክ በነጻ እንደተሰጠው ይናገራል።

ቻክም ባገኘው ትኬት ተጫውቶ የ4 ነጥብ 38 ሚሊየን ዶላር አሸናፊ መሆኑን ተናግሯል።

“ይህንን ያክል ገንዘብ አገኛለው ብዬ አስቤ አላውቅም፤ አሁንም ማመን አቅቶኛል፤ ገንዘቡ የባንክ ሂሳቤ ውስጥ እስኪገባልኝ ድረስም አላምንም” ብሏል ቻክ።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd