የ120 ሚሊየን ዶላር ስልክ የተጠቀመው አሜሪካዊ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩናይትድ ስቴትስ ሚያሚ አንድ አሻሻጭ ግለሰብ ከ90 ሚሊየን የሚበልጡ ግለሰቦች ጋር በመደወል 120 ሚሊየን ዶላር እንደቆጠረበት ተነግሯል፡፡


ይህ ግለሰብ አድርያን አብራሞቪች ይባላሉ፤ ሚሊየኖች ጋር ሊደርሱ የበቁትም ተቀርጾ በተቀመጠ ድምጽ አማካኝነት ነው ተብሏል፡፡

የሀገሪቷ የፌደራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ባለስልጣን በዚህ መጠን ከዚህ ቀደም በማሽን እገዛ ተደውሎ እንደማያውቅ ገልጿል፡፡

አሻሻጩ አብራሞቪች በበኩላቸው ህግን ለመጣስ ሆነ ብለው ያደረጉት ድርጊት ያለመሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውሃ የሚቋጥር መከራከሪያ አይደለም ብሏቸዋል፡፡

በማሽን የሚደወሉት ሁሉም ጥሪዎች ያለተቀባዩ ፍቃድ የሚደወሉ እንደነበሩም ተነስቷል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አብራሞቪች ላይ ሌላ ክስም መዞባቸዋል ማሽኖቹ ወደ ግለሰቦች በሚደውልበት ወቅት አሳማኝ እንዲሆን የአካባቢያቸውን የመነሻ ቁጥር ይጠቀም እንደነበረም ይፋ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ድርጊት ህጋዊ አይደለም፤ አብዛኛው አሜሪካዊም በማሽን እገዛ የሚደወሉ ጥሪዎችን ማንሳት አይፈልግም ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ