የፊት ማስክና አሮጌ ልብስ በመልበስ በሚያስተዳድሯት ከተማ ማንነታቸው ሳይታወቅ ጉብኝት ያደረጉት የማዘጋጃ ቤት ሹም

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣ 15፣ 2010፣( ኤፍ.ቢ.ሲ)የካዛኪስታን ዋና ከተማ መዘጋጃ ቤት ሹም የፊት ገጽታቸውን በሰው ሰራሽ ማስክ በመሸፈንና አሮጌ ልብስ በመልበስ በመዲናዋ የሚከናዎኑ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ሲጎበኙ የሀገሪቱ ሰዎች ማንነታቸውን እንዳላዎቁ ተገለጸ።

የመዘጋጃ ቤቱ ሹም የጺም ማስክ በማጥለቅና አሮጌ ልብሶችን በመልበስ በመዲናዋ በመዘዋዎር እየተከናወቆኑ ያሉ ተግባራትን ሲመለከቱ ማንም ጠያቂ እንዳልነበራቸው ለአገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ተናግረዋል ነው የተባለው።

 በዚህም የቢሼኪክ ከተማ ማዘጋጃ ሹም አልቤክ ኢብራኢሞቭ በመዲናዋ የሚከናዎኑ ሁለንተናዊ ተግባራትን በሪፖርት ወይንም ከ3ኛ ወገን ከመግኘት ይልቅ በቀጥታ ተዘዋውረው ለመመልከት እንዳስቻላቸው ታውቋል።

በከተማዋ ኦሽ ባዛር በተባለው ታላቁ የገብያ ማዕከል በፈረንጆቹ ሚያዚያ 13 ከፍተኛ የእሳት አደጋ የተከሰተና መንስኤው ያልታወቀ ሲሆን፥ አደጋው በዚህ መንገድ ማንነተቻው ባልታወቁ ሰዎች ሊከሰት እንደሚችል ነው ኢብራኢሞቭ ገለጹ የተባለው።

በዚህ አመት ብቻ ለ3 ጊዜ ያህል ተመሳሳይ የእሳት አደጋዎች በመዲናዋ እንደተከሰቱም የመዘጋጃ ቤቱ ሹሙ እስረድተዋል ተብሏል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ upi.com

የተተረጎመና የተጫነው፦ እንቻለው ታደሰ