በሚከተሉት የትምህርት ስርዓት በዓለም ላይ ዝቅተኛውን ደረጃ የያዙ ሀገራት…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣ 15፣ 2010፣( ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት የሰዎችን ህይዎት መሰረት ለማስተካከል ሁነኛ መሳሪያ ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዜጎች መሰረታዊ ትምህርትን ለማደረስ የተለያዩ እንቅፋቶች ያጋጥማሉ።

ከእንቅፋቶች መካከልም የእርስ በእርስ ግጭቶችና ድህነት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሲሆን፥ ለዜጎቹ መሰረታዊ ትምህርት በማድረስ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፋ ችግር ላይ ያሉት ሀገራትን መረጃ ቦርድ አርቲክል ዶት ኮም በድረ ገጹ አስፍሯል።

 በዚህም ቡሪኪና ፋሶ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፓፕሊክ፣ ሴራሊዮን፣ ቡርማ፣ ማሊ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ጊኒ፣ ጂቡቲና ኤርትራ በቅደም ተከተል ዝቅተኛ ደረጃ ላይ በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1- 11 የቀዳሚነት ደረጃቸውን ይዘዋል።


1. ቡሪኪና ፋሶ

ዜጎቹ ከ6 እስከ 7ኛ ክፍል ደረጃዎች ላይ ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡና ከተማሪዎች ቁጥር አንጻር ሲታይ በሀገሪቱ የመምህራን ቁጥር በቂ እንደሆነ የተ.መ.ድ መረጃ እንደሚያመላክት ተገልጿል።
በዚህም በሀገሪቱ 50 በመቶ ያህል ዜጎች ማንበብና መፃፍ የማይችሉ ሲሆን፥ መንግስት ችግሩን ለማቃለል እየሰራ ነው ተብሏል።

2. መካከለኛ አፍሪካ ሪፓፕሊክ

መንግስት ለትምህርቱ ዘርፍ በቂ በጀት ባለመመደቡ ትምህርት ቤቶች እየተዘጉ እንደሆነና ተማሪዎቹ የትምህርት መሳሪያ እጥረት እንዳለባቸው ታውቋል።
በዚህም ተማሪዎች በተከታታይ የትምህርት ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ የተገለጸ ሲሆን፥ መምህራኖችም የሰሩበትን ክፍያ አያገኙም ነው የተባለው።

3. ሴራሊዮን

በርካታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ቢታወቅም 50 በመቶ ያህሉ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፤ ተማሪዎቹ ቢባዛ በትምሀርት ቤት የ3 ዓመታት ያህል ብቻ ቆይታ ሲኖራቸው በሀገሪቱ ማህይምነት እንደተስፋፋ ተጠቁሟል።

4. በርማ

የበርማ ግጭት የትምህርት ስርዓቱ ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል፤ ተማሪዎችም በትምህርት ገባታቸው ላይ እንዳይውሉም ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።
ከዚህም ሌላ መንግስት የዘርፉን በጀት በማቋርጡ በርካታ ጎሳዎች የትምህርት አገልግሎት እንደማያገኙና ህፃናት ከ5ኛ ክፍል በላይ የመማር እድል እንደሌላቸው ነው በዘገባው የተጠቀሰው።

4. ማሊ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገሪቱ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን፥ በርካታ መምህራኖችን ወደ ስራው እንዲቀላቀሉ አድርጋለች ተብሏል።
በዚህም በሀገሪቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሸፋን በፍጥነት እያደገ ቢመጣም በርካታ ተማሪዎች መጨበጥ ያለባቸውን ዕውቀት ገና እንዳላገኙ ነው የተገለጸው።

5. ቻድ

በሀገሪቱ 50 በመቶ ያህል ተማሪዎች 4ኛ ክፍል ሳይደርሱ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ።
በቻድ በትምህርት ቤት ካሉ የተማሪዎች ቁጥር አንፃር በቂ መምህራንና የሰለጠኑ ባለሞያወችም እንዳሉም ታውቋል።
በሀገሪቱ የስደተኞች ጣቢያ በመስፋፋቱም የትምህርትን ሸፋን ለዜጎቹ በማዳረስ በኩል ችግር እንደፈጠረ ነው ዘገባው የተገለጸው ።
6. ኒጀር

በኒጀር ተማሪዎቹ ከ2 ዓመት በላይ በትምህርት ቤት የማይቆዩ በመሆናቸው ዜጎቹ ለማህይምነት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል።
በትምህርት ገበታቸው ላይ ለሚቆዩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪው ከፍተኛ በመሆኑ ትምህርታቸውን ለመቀጠል እንቅፋት እንደሆነም ነው የተጠቀሰው።

7. ጊኒ

ጊኒ ከተማሪዎች ከፍተኛ የትመህርት ክፍያ ከሚጠይቁ ሀገራት አንዷ ስትሆን፥ አብዛኛዎቹ ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪ የሚሸፍኑ ባለመሆናቸው ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡ ታውቋል።

10. ጂቡቲ


ጂቡቲ ተማሪዎቿ ከ4ኛ ወይንም 5ኛ ክፍል በላይ በትምህረት ቤት የማይቆዩባት የምስራቅ አፍሪካ ብቸኛዋ ሀገር እንደሆነች ነው የተገለጸው።
ትምህርት ቤቶችም መጽሀፍትና የመሳሰሉት ግብዓት እና የመምህራን እጥረት ያለባቸው ናቸው ተብሏል።


11. ኤርትራ

በኤርትራ በቅርብ ዓመታት የመምህር እጥረት አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ የተገለጸ ሲሆን፥ ተማሪዎቿም 10ኛ ክፍል ከመድረሳቸው በፊት ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡ ነው ቦርድ አርቲክል ዶት ኮም በመረጃው ያመላከተው።

 

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ boredarticles.com

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ እንቻለው ታደሰ