በአሜሪካ በየዕለቱ 150 ሺህ ቶን ምግብ ይባክናል

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በየዕለቱ 150 ሺህ ቶን ምግብ እንደሚባክን የቅርብ ጊዜ ጥናቶች አመለከቱ።

ይህ ማለት በዓመት በ12 ሚሊየን ሄክታር ላይ ከሚሰበሰበው እህል እኩል እንደሚሆን አጥኚዎቹ አስታውቀዋል።

እንዲሁም የሚጣለው ምግብ 7 በመቶ የሚሆነው ማሳ እንደሚሸፍን ገልጸዋል።

በየዕለቱ  አንድ ግለሰብ 422 ግራም ምግብ እንደሚደፋ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ጥናቱ ያተኮረው ከ2007 እስከ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ በተሰበሰበ መረጃ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ገልጸዋል።

አብዛኞቹ የሚባክኑት ምግቦች ታዲያ አትክልትና ፍራፍሬ ሲሆኑ፥ 39 በመቶውን ይሸፍናሉ ተብሏል።

የወተት ውጤቶች በ17 በመቶ ይከተላሉ፤ የስጋ ውጤቶች በአንጻሩ 14 በመቶውን ይይዛሉ ተብሏል።

ለሰዎች ጤና መልካም እንዲሆን እንዲመገቧቸው ከሚመከሩት ምግቦች መካከል አትክልትና ፍራፍሬ ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ በአንጻሩ ከሚባክኑት መካከል ዋነኛዎቹ መሆናቸው ግርምትን ፈጥሯል።

አጥኚዎቹ በዚህ ጉዳይ ላይ አትክልቶችን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

እንዲሁም በቅርቡ የአውሮፓ ፓርላማ በ2030 የሚባክን ምግብን በ50 በመቶ ለመቀነስ ውሳኔ አሳልፏል።

በተጨማሪም ህብረቱ በዓመት ለሚባክነው 88 ሚሊየን ቶን ምግብ 176 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚወጣ አስታውቋል።

 

 


ምንጭ፦ ሲጂቲኤን
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ