በብሪታኒያ ሮቦቶች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት ስነ ምግባርን መሰረት ያደረገ ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 8፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰዎች ሮቦቶችን ሰዎችን ለመጉዳት፣ ለማጥፋትና ለማጭበርበር ተግባር የመጠቀም ስልጣን መሰጠት እንደሌለባቸው ተገለጸ።

አገልግሎት ሰጪ ሮቦቶች ሲሰሩ ለስነ ምግባር ትልቅ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ነው የተገለጸው።

 የብሪታኒያ ላዕላይ ምክር ቤት ጉዳዩን የሚመለከት አንድ ኮሚቴ ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ብሪታኒያ ሮቦቶችን በሰፊው የመፈብረክና የመጠቀም ፍላጎት አላት ተብሏል።

 ይሁን እንጂ የሰዎቹ መረጃ፣ መብትና ፍላጎት መጠበቅ ላይ ቀደም ብሎ በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው በዘገባው ተገልጿል።

በዚህም በሮቦቶቹ የታገዘ አገልግሎት ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ደንበኞቹ አገልግሎቱን በሮቦቶች የማግኘት ያለማግኘት ፍላጎታቸው መረጋገጥ እንዳለበትም ነው በዘገባው የተገለጸው።

የኮሚቴው ሰብሳቢ ሎርድ ክለመንት ጆንስ እንደገለጹትም ብሪታንኒያ ሮቦቶችን ከነጉድለቶቻቸው ከመቀበል ይልቅ ለሰዎች አወንታዊ አገልግሎትና ጥቅም እንዲሰጡ ዓለም አቀፋዊ ተፈላጊነት እንዲኖራቸው የማድረግ ልዩ የማሻሻል አቅም አላት።

ሰዎች ከስራቸው ጎን ለጎን ሮቦቶችን ለመጠቀም የሚስችላቸው ትምህርት መሰጠት እንደሚያሰፈልጋቸውም ኮሚቴው አስተያየቱን ሰጥቷል።

ለሰዎቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ትምህርት መሰጠቱ ሮቦቶቹን ላልተፈለገ ስራ ማዋሉን ሊቀንሰው እንደሚችልም ተመላክቷል።

በአሁኑ ሰዓትም ቀደም ሲል የነበሩ በርካታ የሮቦት ስራዎች የጠፉና አዲስ ተግባራት የተፈጠሩ በመሆኑ ሮቦቶቹ መሻሻል ያለባቸው እንደሆነ ሪፖርቱ ያሳያል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ የሀገሪቱ መንግስት ስልጠና በመስጠት የዜጎችን ህይወት በቴክኖሎጂ ለማገዝ መስራት እንዳለበትም ተገልጿል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

የተተረጎመና የተጫነው፦ እንቻለው ታደሰ