በየዓመቱ ሴት ጓደኛውን ለማግኘት ከ14 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚጓዘው ወፍ

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2010 (ኤፍቢሲ) በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን አቅራቢያ መካከልና በአውሮፓዊቷ ክሮሺያ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ ረዣዥም እግርና አንገት ያለው የወፍ ዝርያ ለሴት ፍቅረኛው የሚከፍለው መስዋእትነት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

ይህ ወፍ መብረር የማትችለውን ሴት ወፍ ለመጎብኘት በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠር ኪሎ ሜትር እየበረረ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ክሮሺያ ይጓዛል።

ተመላላሹ ወንድ ክሌፕታን በመባል ይጠራል፤ ሴቷ መብረር የማትችለው አካል ጉዳተኛ ደግሞ ማሌና ትባላለች።

ታማኙ ክሌፕታን በየዓመቱ በበጋ ወራት ከደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ማሌናን ለማየት ወደ ክሮሺያ ያቀናል።

ታዲያ በዚህ ዓመትም ክሌፕታን ባለማቋረጥ ለ16 ተከታታይ ዓመታት ማሌናን የጠየቃት ሲሆን፥ ብዙ ልጆችንም ማፍራት ችለዋል።

በሁለቱ አገራት መካካል የ14 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለ ሲሆን፥ ወንዱ ወፍ ከደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ክሮሺያ ለመድረስ ወር ገደማ ይወስድበታል።

እነዚህ ስቶርክ በመባል የሚታወቁት ወፎች ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ክሮሺያ ለመድረስ ከአንድ ወር በላይ ይፈጅባቸዋል ነው የተባለው።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1993 ላይ ወደ ክሮሺያ ፈልሰው ከነበሩት አሞራዎች መካከል ማሌና በአዳኞች ጉዳት ደርሶባት አንድ ሀይቅ አካባቢ ትወድቃለች።

በዚህ ወቅት ታዲያ አንድ ስቴፋን የተባሉ ክሮሺዊ ያገኙዋትና እንክብካቤ ያደርጉላታል።

የ71 ዓመቱ ስቴፋን እንዲህ ይላሉ "ወደ አፍሪካ ባልወስዳትም አሳ ለማስገር አብረን እንሄዳለን ቴልቪዥንም አብረን እንመለከታን" ብለዋል።

1-stjepanvokic.jpg

malenawaitsi.jpg

 

 

እንዲሁም ለህይወቷ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ እየተንከባከቧት እንደሚገኙ ነው የተናገሩት።

በፀደይ ወቅት ስቴፋኒ ትልቅ ጉጆ ለሜላኒ እንደሚሰሩላት የገለጹ ሲሆን፥ ክሌፕታን ደግሞ በነሃሴ ወር ወደ ደቡብ አፍሪካ ከመመለሱ

በፊት ልጆቹን በረራ እንደሚያስተምርም ተናግረዋል።

ሁለቱ ወፎች ፍቅራቸው በሀገረ ክሮሺያ እጅግ ታዋቂነትን አትርፎላቸዋል ነው የተባለው።

ክሮሺያ በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 500 የሚደርሱ ጥንድ ስቶርኮች መኖሪያ ናት።

 

 

 


ምንጭ፦ኤኤፍፒ
በአብርሃምፈቀደወደአማርኛተመለሰ