በፓሪስ ሁለት የዳይኖሰር አጽሞች በ3 ሚሊየን ዶላር ተሸጡ

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2010 (ኤፍቢሲ) በፓሪስ በተደረገ ጨረታ ሁለት የዳይኖሰር አጽሞች 3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መሸጣቸው ተገለጸ።

እስከ አሁን ድረስ የገዢዎቹ ማንነትና ዜግነት በይፋ አልተነገረም ተብሏል።

የሁለቱ ዳይኖሰሮች 12 ሜትር ርዝመት እና ሶስት ነጥብ ስምንት ሜትር ቁመት እንዳላቸው ተገልጿል።

እነዚህ ሁለት ዳይኖሰሮች በጁራሲክ ዘመን የነበሩ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፥ ይህም ከ150 ሚሊየን በላይ ዓመታት ያስቆጠሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በዓለም ላይ የዓመቱ አምስት የዳይኖሰር አጽሞች ለጨረታ ይቀርባሉ።

አብዛኛዎች እጅግ ሐብታም በሆኑ ግልሰቦችና ውድ ዕቃ በመሰብሰብ በሚታወቁ የአውሮፓ ሙዚየሞች ግብይቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ቅሪተ አካሎችን የሚሸጠው ባለሙያ ላኮፖ ብሪያኖ ልክ እንደ ስዕል የዳይኖሰር አጽሞችን መሰብሰብ አዲስ አካሄድ ሆኗል ብሏል።

ባለሙያው የሆሊውድ ፊልም አክተሮች ሊዮናርዶ ዲካፕሮና ኒኮላስ ኬጅ ቅድመ ታሪክ የሆኑ ጌጣጌጦችንና መሰል ነገሮችን ከሚሰበስቡ መካከል መሆናቸውን ጠቅሷል።

 

 

ምንጭ፦ ኢንዲያታይምስ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ