በፀሀይ ብርሀን ወቅት መንቀሳቀስ የማይችለው ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2010(ኤፍ ቢ ሲ) የጨረቃ ልጅ ተብሎ ምትክ ስም የወጣለት ይህ ታዳጊ ባለበት የፀሀይ አለርጂ ምክንያት የፕላስቲክ ልብስ ሳይለብስ ወደ ፀሀይ ብርሃን መውጣት እንዳማይችል ተነግሯል።

ታዳጊው ያለበት የፀሀይ አለርጂ በአሜሪካ ከሚገኙ 1 ሚሊየን ህፃናት በአንዱ ብቻ የሚከሰት ነው።

ህፃኑ የ18 ወር ልጅ በነበረበት ወቅት ለበሽታው የተጋለጠ ሲሆን፥ ቆዳው ለፀሀይ ብርሀን ከተጋለጠ ጥቁር ነጠብጣብ በማውጣት ወደ ነበረበት መመልስ እንደማይችል ተነግሯል።

ኦሊቨር ኪ የተባለው የሰባት ዓመት ህፃን ከሌሎች ሰዎች በተለየ 1 ሺህ እጥፍ ለቆዳ ካንሰር ተጋላጭ እንደሆነም ታውቋል።

ኦሊቨር በፀሀይ ብርሀን ወቅት መቀሳቀስ ሲያስፈልገውም ወፍራም የፕላስቲክ ልብስና ጓንት መጠቀም እንዳለበት ተነግሯል።

ይህ ህፃን በፀሀይ ብርሀን ወቅት ቆዳው የሚጠቁር ሲሆን በዚህም ለቆዳ ካንሰር የሚያጋልጡ ምልክቶች በሰውነቱ ላይ እንደሚወጡ ታውቋል።

በዚም ምክንያት የህፃኑ መኖሪያ ቤት እና መኪና የፀሀይ ብርሃን መከለከያ የተገጠመለት ሲሆን የመኝታ ቤት መብራትም ቆዳውን እንዳይጎዳው ጥንቃቄ ይደረጋል ተብሏል።

ህፃን ኦሊቨር ምሽትን ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን በጨዋታ ስለሚያሳልፈው በጉጉት እንደሚጠብቀውና ደስተኛ እንደሆነ ይናገራል።

በዚህ የፀሀይ ብርሃን አለርጂ የተጋለጡ ህፃናት በአብዛኛው የአለም ክፍል “የጨረቃ ልጅ” በመባል ይታወቃሉ።

ምንጭ፦ ፎክስኒውስ