ከ14 ዓመታት መጥፋት በኋላ ባለቤቷን ያገኘችው ድመት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ከ14 ዓመታት በፊት የጠፋችቦት ድመት ተግኝታለችና መጥተው ይረከቡን ቢባሉ ምን ይላሉ?

በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ከ14 ዓመታት በፊት ከጠፋችው ድመቱ ጋር መገናኘቱ ነው የተነገረው።

ድመቷ የተሰወረችው በአካባቢው በሰዓቱ ተከስቶ በነበረ ዝናብ በቀላቀለ አውሎንፋስ ምክንያት ነው።

ከእንስሳ ማቆያ ማዕከል "ድመትህ ተገኝታለች ብንልህ ምን ይሰማሃል" ብለው በስልክ ላቀረቡለት ጥያቄ "እሷ ከሞተች ረዥም ጊዜ ነው ምናልባት አብዳችሁ ይሆናል" ማለቱ ተገልጿል።

የድመቷ ባለቤት ማርቲን ይባላል፤ በወቅቱ ቢሮ ሆኖ ስለድመቷ መገኘት በእርግጠኝነት ተደውሎ ሲነገረው እጅግ መደንገጡን ተናገሯል።

ማርቲን "ልክ እንደየኋት ቲ2 መሆኗን አወቅሁ ትንሽ አርጅታለች ልክ እንደኔ" ብሏል።

ቲ2 የተገኘችው መንገድ ላይ መሆኑን ማዕከሉ ገልጿል።

ከቤተሰቧ ጋር ዳግም የመቀላቀል ዕድል አግኝታለች፣ ትበላለች፣ ቤት ውስጥ ትዞራለች በዚህም እጅግ ደስተኛ ነኝ ብሏል።

 

 

 

ምንጭ፦ ምንጭ፦ ዩፒአይ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ