ለሞባይል ቪዲዮ ጨዋታ እስከ 70 ሺህ ዶላር ወጪ የሚያደርገው ጃፓናዊ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነጻ የሞባይል መጫዎቻ ቪዲዮች ያሉ መሆኑ ይታወቃል፣ ነገር ግን አንዳንድ መተግበሪያዎች ለፈጠራ ባለመብቶቻቸው የገቢ ምንጭ ሆነዋል። 

 

ዲያጎ የተባለው የ31 ዓመት ጃፓናዊ የሞባይል ቪዲዮ ጨዋታ ተጠቃሚ ለዚሁ ተግባር 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጭ እንዳደረገ ተሰምቷል።

የሶኒ ክሮፕ “ፌት ወይም ግራንድ ኦርደር” የተባሉት የሞባይል ቪዲዮ መጫዎቻ መተግበሪያዎች ያሉ ሲሆን፥ መተግበሪያዎቹ በነጻ የምናውርዳቸውና የምንጠቀማቸው ናቸው።

በዚህ ተግበር በያዝነው በጀት ዓመት እስከዚህ ወረ መጨረሻ ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚገመት ገቢ ይገኛል ቢባል የሚታመን አይደልም።

ይሁን እንጂ እንደነ ዲያጎ ያሉ ተጫዋቾች፣ የጨዋታ ፍጥነታቸውንና ብቃታችውን ለማሻሻል ወጪ ከሚያደርጉት ገንዘብ አንጻር የሚቻል ሆኖ ተገኝቷል ነው የተባለው።

የ31 ዓመቱ ጃፓናዊው ለዚህ ለሚወደው የሞባይል ቪዲዮ ጨዋታ ከ70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዳወጣ ይገምታል።

ፌት/ግራንድ ኦርደረ ለዲያጎ ሱስ ሆኗል ቢበል ቃሉ በትክከል አይገልጸውም፤ ጨዋታውን የሚያቆመው ሲተኛ፣ መኪና ሲያሽከረሽ ወይንም መታጠቢያ ቤት ሲገባ ብቻ ነው።

ዲያጎ ለወዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ እንደገለጸው “አንዳንደ ሰዎች እስከ 18 የአሜሪካ ዶላር ለፊልም በማውጣት ይዝናናሉ፤ እሱም ለፌት/ እለሞባይል ጨዋታው የማወጣው ልክ ሌሎቹ በፊልም እንደሚዝናኑት ነው ብሏል።

በመጀመሪያዎቹ ምእራፎቸ መጫወት ስንጀምር አብዛኞቻችን በደስታ አንብተናል፣ ታሪኩ ወደ እያንዳዶቻችን ማንነት የቀረበ ነው፣ የሆነ ነገር እንዲሰማንም አድርጓል፤ የምትወደውን ትፈልገዋለህና እኛም ጨዋታውን ለመድነው ሲል አስረደቷል።

ፌት /ግራንድ ኦርደረ ጨዋታ አንዴ ከጀመሩት እራሱ ጨዋታው ተጨዋቾቹን ይቆጣጠራል የተባለ ሲን፥ ይህም ተጫዋቾች ገንዘባቸውን ኳርቲዝ ወደ ተባለው የቪዲዮ ጨዋታው ክፍያ በመቀየው በመቀየር ገቢ ያደርጋሉ።

ክፍያው የሚፈጸመው በኤለክቴሮኒክ የክፍያ ዘዴ ሲሆን፥ የቸኮለና የጨዋታ ብቃቱን ቶሎ ለማሻሻል ከፍተኛ ጉጉት ያደረበት በጥሬ ከንዘብም መከፈል የሚችል መሆኑንም በዘገባው ተገልጿል።

ዲያጎ የሚፈልገውን ሌላ ተጨማሪ የጨዋታ አይነት በቪዮ ማጫዎቻው ለማካተት 500 የአሜሪካ ዶላር እንዳወጣ ያስታውሳል፤ የበለጠ የማጫዎቻ ቪዶውን ለማሟላትና ለማጠናከረ ሌላ 2 ሺህ 500 ዶላር እንደሚያሰፈለገውም ተናግሯል።

 

 

ምንጭ፣ ኦዲቲ ሴንትራል

የተተረጎመና የተጫነው በእንቻለው ታደሰ